መመርያ ደንብ
- ንፁህ ሸሚዝ እና በደንብ የተተኮሰ ሱሪ ልለብስ
- ተሳፋሪን ከ ማገልገሌ በፊት መኪናዬን ከ ውስጥም ሆነ ከ ውጭ በ የቀኑ ላፀዳ
- ተሳፋሪን በ ቀና አመለካከት እና በስላሳ አቀራረብ ላገለግል
- የ ተሳፋሪውን ምቾት እና የጋራ ደህንነት በደገፈ መልኩ ተጠንቅቄ ላሽከረክር
- ለ ደህንነት እና ለምቾት ሲባል ተሳፋሪዬን ከጀርባ እንዲቀመጥ በትህትና ላሳስብ :: ከፊት ለመቀመጥ ቢመርጥ ግን እንደ ምርጫው ላስተናግድ
- በ አገልግሎት ወቅት ስልኬ ለተሳፋሪ በሚታይ መልኩ ማስቀመጫ ላይ ላኖር
- ተሳፋሪዬን ስለ ግል ችግሬ በጨዋታ ማጥመድ ሳይሆን ፣ ስሜትን ተረድቶ በቀናነት ላስተግባ እና ምቾትን ልሰጥ
- ሻንጣ ወይም የተፈቀደን እቃ መኪና ውላይ ለመጫን ያለ ምንም ማዳላት ተሳፋሪን በቀናነት ላግዝ
- በ ማንኛውም ግዜ ተሳፋሪዬ ሬድዮ ላይ ምን ማዳመጥ እንደሚፈልግ እና የድምፁን መጠን በማመጣጠን ልተባበር
- ከ አንድ በላይ አማራጭ መንገዶች ካሉ ከ መነሳቴ በ ፊት ተሳፋሪን አማራጭ ልሰጥ (አላስፈላጊ የርቀት ክርክርን ያስወግዳል)
- መኪናዬን ለ አረጋውያን ፣ ለታካሚዎች ወይም ለአካል ጉዳተኞችምቹ እንዲሆን በመደገፍ እንደ አስፈላጊነቱ ልተባበር
- በ ዝናብ ወቅት ዣንጥላ በመያዝ ተሳፋሪን ያለ ምንም አድልዎ ላገለግል
- ሁልግዜ አገልግሎት በ ተፈለገ በ 10 ደቂቃ ውስጥ ልደርስ :: ቀድሞ ለተያዙ ትዕዛዞች ከ 10 ደቂቃ በፊት ልደርስ :: ይህ መሆን ካልተቻለ ግን ለ ራይድ በ ስልክ ወዲያው የ አገልግሎት ለ ውጡን ላሳውቅ::
- የ ሚያዘገይ ሁኔታ ቢፈጠር ተሳፋሪውን ወዲያው በመደወል ላሳውቅ እና ላማክር
- በ ጥንቃቄ እና በ ተፈቀደልኝ ህጋዊ ፍጥነት ላሽከረክር
- አደጋን ለማስወገድ ፣ ከደከመኝ አረፍ ልል
- የ መቀመጫ ቀበቶ በ አገልግሎት ወቅት ላስር :: ደንበኛው ከ ፊት ለ ፊት ለመቀመጥ ቢፈልግ ቀበቶ እንዲያስር በትህትና ላሳስብ
- በ ትራፊክ መጨናነቅ ወይም ፀባያቸው በ ማይስማማ ተሳፋሪዎች ሊከሰት የሚችልን ማንኛውም ጭቅጭቅ በ ሰከነ መንፈስ ልፈታ
- ከ ራይድ ለ ሚመጣ ጥሪ አፕልኬሽኑ ካሰላው ዋጋ በላይ ተሳፋሪን ላልጠይቅ
- ምንም አይነት አልኮሆል ጠጥቼ ተሳፋሪን ላላስተናግድ
- ጨለማ በሆነ አካባቢ ብርሃን በማብራት ተሳፋሪዬ እቤት እስኪገባ ልጠብቅ
- ማንኛውም አይነት መጥፎ ጠረንን ከ መኪናው ውስጥ ላስወግድ
- በ ምንም አይነት መልኩ መኪናዬ ውስጥም ሆነ ውጭ ከ ራይድ ፈቃድ ያልተሰጣቸውን ቴክኖሎጂነ ክመተግበሪያዎች ላልጠቀም : :
- ከ ራይድ ባገኘሁት ስልክ ላይ ምንም አይነት አፕልኬሽን ከ ራይድ የ ፅሁፍ ፈቃድ ውጭ ላልጭን
- የ ራይድ የ ግል አካውንቴን ያለ ራይድ የ ፅሁፍ ፈቃድ ለ ሌላ ሰው አሳልፌ ላልሰጥ
- መኪናዬን አቁሜ ስልክም ሆነ የራይድን አፕልኬሽን ልጠቀም ፣ በ እንቅስቃሴ ወቅት የ ራይድ መተግበሪያዬን ‘Offline’ ላይላኖር
- የመኪናም ሆነ የአሽከርካሪ ህጋዊ ሰነዶችን በማንኛውም ሰዓት አሟልቼ ልገኝ
- ከራይድ በየግዜው የሚወጡትን መመሪያዎች ልከታተል እና በየግዜው በሃላፊነት ልተገብር
- በተሰጠኝ ህጋዊ ፈቃድ መሰረት ከራይድ ጋር የኪራይ አገልግሎት ብቻ ልሰጥ
- በምዝገባ ወቅት በራይድ የተፈቀደልኝን መኪና ብቻ ይዤ ተሳፋሪ ላጓጉዝ:: አፕልኬሽኔ ላይ የተመዘገበው የታርጋ ቁጥር ከማሽከረክረው መኪና ጋር አንድ መሆኑን ላረጋግጥ
በማጠቃለያነት
-
ተሳፋሪ ጋር በ10 ደቂቃ ውስጥ ይድረሱ:: ከአቅም በላይ ከሆነ ደውለው እንዲጠብቁ በትህትና ያስተማምኑ
-
የተሳፋሪን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ቀና መስተንግዶ ይስጡ
-
የመኪናዎንና የግል ንፅህናዎን ይጠብቁ