Ethiopia's Pride

RIDE Driver Terms

መመርያ ደንብ

  1. ንፁህ ሸሚዝ እና በደንብ የተተኮሰ ሱሪ ልለብስ
  2. ተሳፋሪን ከ ማገልገሌ በፊት መኪናዬን ከ ውስጥም ሆነ ከ ውጭ በ የቀኑ ላፀዳ
  3. ተሳፋሪን በ ቀና አመለካከት እና በስላሳ አቀራረብ ላገለግል
  4. የ ተሳፋሪውን ምቾት እና የጋራ ደህንነት በደገፈ መልኩ ተጠንቅቄ ላሽከረክር
  5. ለ ደህንነት እና ለምቾት ሲባል ተሳፋሪዬን ከጀርባ እንዲቀመጥ በትህትና ላሳስብ :: ከፊት ለመቀመጥ ቢመርጥ ግን እንደ ምርጫው ላስተናግድ
  6. በ አገልግሎት ወቅት ስልኬ ለተሳፋሪ በሚታይ መልኩ ማስቀመጫ ላይ ላኖር
  7. ተሳፋሪዬን ስለ ግል ችግሬ በጨዋታ ማጥመድ ሳይሆን ፣ ስሜትን ተረድቶ በቀናነት ላስተግባ እና ምቾትን ልሰጥ
  8. ሻንጣ ወይም የተፈቀደን እቃ መኪና ውላይ ለመጫን ያለ ምንም ማዳላት ተሳፋሪን በቀናነት ላግዝ
  9. በ ማንኛውም ግዜ ተሳፋሪዬ ሬድዮ ላይ ምን ማዳመጥ እንደሚፈልግ እና የድምፁን መጠን በማመጣጠን ልተባበር
  10. ከ አንድ በላይ አማራጭ መንገዶች ካሉ ከ መነሳቴ በ ፊት ተሳፋሪን አማራጭ ልሰጥ (አላስፈላጊ የርቀት ክርክርን ያስወግዳል)
  11. መኪናዬን ለ አረጋውያን ፣ ለታካሚዎች ወይም ለአካል ጉዳተኞችምቹ እንዲሆን በመደገፍ እንደ አስፈላጊነቱ ልተባበር
  12. በ ዝናብ ወቅት ዣንጥላ በመያዝ ተሳፋሪን ያለ ምንም አድልዎ ላገለግል
  13. ሁልግዜ አገልግሎት በ ተፈለገ 10 ደቂቃ ውስጥ ልደርስ :: ቀድሞ ለተያዙ ትዕዛዞች 10 ደቂቃ በፊት ልደርስ :: ይህ መሆን ካልተቻለ ግን ለ ራይድ በ ስልክ ወዲያው የ አገልግሎት ለ ውጡን ላሳውቅ::
  14. የ ሚያዘገይ ሁኔታ ቢፈጠር ተሳፋሪውን ወዲያው በመደወል ላሳውቅ እና ላማክር
  15. በ ጥንቃቄ እና በ ተፈቀደልኝ ህጋዊ ፍጥነት ላሽከረክር
  16. አደጋን ለማስወገድ ፣ ከደከመኝ አረፍ ልል
  17. የ መቀመጫ ቀበቶ በ አገልግሎት ወቅት ላስር :: ደንበኛው ከ ፊት ለ ፊት ለመቀመጥ ቢፈልግ ቀበቶ እንዲያስር በትህትና ላሳስብ
  18. በ ትራፊክ መጨናነቅ ወይም ፀባያቸው በ ማይስማማ ተሳፋሪዎች ሊከሰት የሚችልን ማንኛውም ጭቅጭቅ በ ሰከነ መንፈስ ልፈታ
  19. ከ ራይድ ለ ሚመጣ ጥሪ አፕልኬሽኑ ካሰላው ዋጋ በላይ ተሳፋሪን ላልጠይቅ
  20. ምንም አይነት አልኮሆል ጠጥቼ ተሳፋሪን ላላስተናግድ
  21. ጨለማ በሆነ አካባቢ ብርሃን በማብራት ተሳፋሪዬ እቤት እስኪገባ ልጠብቅ
  22. ማንኛውም አይነት መጥፎ ጠረንን ከ መኪናው ውስጥ ላስወግድ
  23. በ ምንም አይነት መልኩ መኪናዬ ውስጥም ሆነ ውጭ ከ ራይድ ፈቃድ ያልተሰጣቸውን ቴክኖሎጂነ ክመተግበሪያዎች ላልጠቀም : :
  24. ከ ራይድ ባገኘሁት ስልክ ላይ ምንም አይነት አፕልኬሽን ከ ራይድ የ ፅሁፍ ፈቃድ ውጭ ላልጭን
  25. የ ራይድ የ ግል አካውንቴን ያለ ራይድ የ ፅሁፍ ፈቃድ ለ ሌላ ሰው አሳልፌ ላልሰጥ
  26. መኪናዬን አቁሜ ስልክም ሆነ የራይድን አፕልኬሽን ልጠቀም ፣ በ እንቅስቃሴ ወቅት የ ራይድ መተግበሪያዬን ‘Offline’ ላይላኖር
  27. የመኪናም ሆነ የአሽከርካሪ ህጋዊ ሰነዶችን በማንኛውም ሰዓት አሟልቼ ልገኝ
  28. ከራይድ በየግዜው የሚወጡትን መመሪያዎች ልከታተል እና በየግዜው በሃላፊነት ልተገብር
  29. በተሰጠኝ ህጋዊ ፈቃድ መሰረት ከራይድ ጋር የኪራይ አገልግሎት ብቻ ልሰጥ
  30. በምዝገባ ወቅት በራይድ የተፈቀደልኝን መኪና ብቻ ይዤ ተሳፋሪ ላጓጉዝ:: አፕልኬሽኔ ላይ የተመዘገበው የታርጋ ቁጥር ከማሽከረክረው መኪና ጋር አንድ መሆኑን ላረጋግጥ

በማጠቃለያነት

  1. ተሳፋሪ ጋር በ10 ደቂቃ ውስጥ ይድረሱ:: ከአቅም በላይ ከሆነ ደውለው እንዲጠብቁ በትህትና ያስተማምኑ

  2. የተሳፋሪን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ቀና መስተንግዶ ይስጡ

  3. የመኪናዎንና የግል ንፅህናዎን ይጠብቁ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Share:

More Posts

2016 E.C. New Year Message from our CEO

የራይድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት:-

እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: መጭው ዓመት በሃገራችን የሰላም- የፍቅር እና የበረከት አመት እንዲሆን በመላው የራይድ ቤተሰብ ስም እየተመኘው- ቤተሰባዊ ወዳጅነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም በቀናነት የምንተሳሰብበት ዘመን እንሚሆን እምነቴ ነው:: ራይድ የሁላችንም ነው! ስለሆነም- በመጭው ዓመት አገልግሎታችንን ሙሉ ለሙሉ ሰው ተኮር በማድረግ በአለም ተወዳዳሪ የሆነና የአፍሪካ ኩራት የሆነ ጠንካራ ድርጅት በጋራ እንደምንገነባ እተማመናለሁ:: መልካም በዓል ከእነቤተሰብዎ እመኛለሁ::

RIDE Company Profile

Hybrid Designs PLC is a revolutionary Mobility technology company that aspires to implement simple, practical, and efficient mobility systems in Africa. Our

Send Us A Message

Scroll to Top