የአሽከርካሪዎች የስምምነት መርሆች (Driver Terms and Conditions)

የመኪና አሽከርካሪዎች ወይም ሳይክሊስቶች በራይድ የቀረቡ የትራንስፖርት እና የምግብ ማመላለሻ ቴክኖሎጂዎችን በሚስጥራዊ ኮድ (OTP) ወይንም ማረጋገጫ (Verification) ገብተው (Login አድርገው) ሲጠቀሙ እነዚህን መርሆች (Terms and Conditions) ፈቅደው ለመተግበር እንደተስማሙ ይቆጠራል:: ይህንንም ለማጠናከር የአሽከርካሪ አፕልኬሽን ውስጥ መግቢያ ቅፅ ላይ ይህንን መርህ እንዲቀበሉ በግልፅ ምርጫ (Selection) ተቀምጦ የሚገኝ ሲሆን ያንን ምርጫ ካልተስማሙ ወደ አፕልኬሽኑ አለመግባት እና አለመጠቀም ሙሉ መብትዎ እንደተጠበቀ ነው:: በተጨማሪም ምዝገባ ካከናወኑ በሁዋላ ለራይድ ድርጅት ክፍያ መፈፀም ለእነዚህ መርሆች ተገዥነትን ያመላክታል:: ይህንን መግለጫ ከተቀበሉ ከስር የተዘረዘሩት መርሆች ከራይድ አካውንት ተቀብለው ሲያገለግሉ ገዥ ስምምነት ሁነው ያገለግላሉ::

አገልግሎት አሰጣጥ እና ጠቅላላ መመርያ

  • አሽከርካሪው በራይድ መተግበሪያ ቴክኖሎጂ ብቻ የሚቀርብለትን የትራንስፖርት ጥሪ በመቀበል አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በፍጥነት ያቀርባል፣
  • መኪናውን የሚያሽከረክረው ከባለቤቱ ውጭ ተቀጣሪ አሽከርካሪ ከሆነ ይህንን የሚያሳይ ህጋዊ የቅጥር ውል ያቀርባል፣
  • በተመዘገበው መኪና አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ አሽከርካሪው የሚከተሉትን ማከናወን ይጠበቅበታል፡-
    • ንፁህ ሸሚዝ እና ሱሪ መልበስ፣
    • የኪራይ መኪናውን ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ጽዳትና ውበት መጠበቅ፣
    • ተሳፋሪውን በቅንነት እና ረጋ ባለ መልኩ የማናገር እንዲሁም ማስተናገድ፣
    • ተሳፋሪውን ምቾት እና የጋራ ደህንነት በጠበቀ መልኩ በጥንቃቄ ማሽከርከር፣
    • ተሳፋሪ ወደ ተሽከርካሪው ከመግባቱ በፊት ደኅንነቱና ምቾቱ የሚጠበቀው ከኋላ ወንበር ሲቀመጥ እንደሆነ በትህትና የማሳሰብ፤
    • ተሳፋሪው ማሳሰቢያውን ከሰማ በኋላ ከፊት ወንበር ላይ ለመቀመጥ ከመረጠ የተሳፋሪውን ምርጫ መቀበልና፣አገልግሎቱን በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ ተንቀሳቃሽ ስልኩን ተሳፋሪው በቀላሉ ሊያየው በሚችልበት ቦታ በስልክ ማስቀመጫ ላይ ማስቀመጥ፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ የግል ችግር ለተሳፋሪ ያለማጫወት፣
    • በተሳፋሪዎች መካከል ልዩነት ወይም መድሎ ሳያሳድር የተሳፋሪዎቹን ሻንጣ ወይም በተሽከርካሪው ላይ ለመጫን የተፈቀደላቸውን ዕቃ ሲጭኑ በቅንነት የማገዝ፣
    • በጉዞ መስመር ላይ ተሳፋሪው ወደሚደርስበት ስፍራ ለመጓዝ ከአንድ በላይ አማራጭ መንገዶች ካሉ ጉዞውን ከመጀመሩ በፊት ተሳፋሪው በየትኛው አማራጭ ሊጓዝ እንደሚፈልግ የመጠየቅ እና ከአማራጭ መንገዶቹ አጭሩን የጉዞ መስመር መርጦ የመጓዝ፣
    • ተሳፋሪዎቹ አረጋውያን፣ እርጉዝ ሴት፣ ታካሚዎች ወይም አካል ጉዳተኞች ወይም ድጋፍ የሚሹ ማናቸውም ሰዎች ከሆኑ ለመሳፈርም ሆነ ለመውረድ እንደሚመቻቸው ተገቢውን ድጋፍ፣ እንክብካቤና ፍቅር በመለገስ ያለአድሎ ትብብር የመስጠት፣
    • አገልግሎት በተጠየቀ በ10 ደቂቃ ውስጥ ወደ ተሳፋሪው የመድረስ፣ ቀድሞ ለተያዙ ትዕዛዞች ከ10 ደቂቃ በፊት ተሳፋሪው ወዳለበት የመድረስ፣ በ10 ደቂቃ ውስጥ ወይም ቀደም ብሎ ተሳፋሪው ወዳለበት ለመድረስ የማያስችል፣ ካቅም በላይ የሆነ እክል ከገጠመው ለራይድ የስልክ ጥሪ ማዕከል የአገልግሎት ለውጡን ቀደም ብሎ ከ20 ደቂቃ በፊት የማሳወቅ እና ወደ ተሳፋሪው ስልክ በመደወል የማሳወቅ እና የመመካከር፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ በጥንቃቄና በትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንቦች በተፈቀደ ሕጋዊ የፍጥነት ወሰን የማሽከርከር፣
    • ደኅነንቱና ምቾቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት በአካልና በመንፈስም ዝግጁ ለመሆን ያስችለው ዘንድ የድካም ስሜት በተሰማው ጊዜ በቂ እረፍት የማድረግ፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ የደኅነነት ቀበቶ (ሲት ቤልት) የማሰር እና ተሳፋሪው በፊተኛው ወንበር ለመቀመጥ ከመረጠ የደኅነነት ቀበቶ (ሲት ቤልት) እንዲያሥር በትህትና የማሳሰብ፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በትራፊክ መጨናነቅ፣ ፀባያቸው ወይም ባህሪያቸው የማይስማማ ተሳፋሪዎች በመጫኑ ወይም በሦስተኛ ወገኖች ድርጊት መነሻነት በተሳፋሪዬ እና በእኔ በአሽከርካሪውም መካከል አለመግባባት ወይም የስሜት መጋል ከተከሰተ አለምግባባቱን በሰከነ መንፈስ የመፍታት እና በጊዜው ለጥሪ ማዕከል ማሳወቅ፣
    • ከአቅራቢው ለሚመጣ ጥሪ የራይድ ቴክኖሎጂ ከሚያሰላው የአገልግሎት ዋጋ በላይ ተሳፋሪን ያለመጠይቅና ያለማስከፈል፣  የቴክኒካል ብልሽት ካጋጠመው ወይም ከተሳፋሪ ቅሬታ ከተነሳ ከማስከፈል በፊት ለጥሪ ማዕከል የማሳወቅ፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ በማሽከርከር አካላዊም ሆነ አዕምሮአዊ ብቃት ወይም በባህሪ ወይም በሁለቱም ላይ ተጽዕኖ ማድርግ ከሚችሉ ማናቸውም የአልኮል መጠጥ፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕጽ ወይም ማናቸውም ነገር ነጻ ሆኖ የመገኘት፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ ተሳፋሪ የሚወርደው ጨለማ በሆነ አካባቢ ከሆነ የተሽከርካሪን ወይም ሌላ ማናቸውም መብራት በማብራት ተሳፋሪ ወደሚገባበት ስፍራ እስኪገባ ቆሞ የመጠበቅ፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት በማናቸውም ጊዜ ተሽከርካሪን ከማንኛውም መጥፎ ጠረን የጸዳ የማድረግ፣
    • አገልግሎት በሚሰጥበት ማናቸውም ጊዜ ለሚሰጠው አገልገሎት በተሸክርካሪ ውስጥም ሆነ ውጪ ከራይድ ፈቃድ ያልተሰጣቸውን ተቀናቃኝ ወይም የጥቅም ግጭት የሚፈጥሩ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽንስ) ያለመጠቀም፣
    • ከአቅራቢው የፅሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ ለሚሰጠው የትራንስፖርት ጥሪ አገልገሎት ከራይድ በተቀበለው ስልክ ላይ ምንም አይነት የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽንስ) ያለመጫን እና ከራይድ ሥራ ውጪ ያለመጠቀም፣

የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ

  • አገልግሎት ሰጪው ለደንበኛ አገልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ለራይድ ድርጅት ክፍያ የሚፈፅም ይሆናል፦
    • አሽከርካሪው በ 1 ወር ውስጥ በጠቅላላ ከ30 በላይ ስራዎችን ካከናወነ በጥቅሉ 12% + ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፣ በወር በጠቅላላው ከ30 በታች ስራዎችን ብቻ ካከናወነ 200.00 ብር የአገልግሎት ክፍያ (Subscription Fee) የሚከፍል ይሆናል::

በመርሁ ተገዥነት ስለሚቋረጥበት ሁኔታና ስለ ቅጣት

  • ራይድ የአሽከርካሪውን መተግበሪያ አካውንት በሚከተሉት ምክንያቶች ሊቋረጥ ይችላል
    • አገልግሎት ሰጪው በዚህ መርህ ውስጥ የተጣሉበትን ግዴታዎች ያለበቂ ምክንያት ሳይፈጽም ከቀረ ራይድ በማንኛውም ግዜ አፕልኬሽኑን ሊያቋርጥ ይችላል
    • ገልጋዮች አገልግሎት ሰጪውን በተመለከተ ቅሬታ ካቀረቡበት፣ ቴክኖሎጂ አቅራቢው የቀረበውን አቤቱታ በማጣራት ጥፋት ነው ብሎ በማስረጃ ከደረሰበት ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ በተናጥል አፕልኬሽኑን ሊያቋርጥ ይችላል
    • አገልግሎት ሰጭ ለአቅራቢው ሳያሳውቅ ያለ በቂ ምክንያት ለሁለት ወር ያህል ምንም ጥሪ ካልተቀበለ አቅራቢው አፕልኬሽኑን ሊያቋርጥ ይችላል
    • አሽከርካሪው በማንኛውም ግዜ ከ ራይድ መተግበሪያዎች ወጥቶ ከስልኩ ላይ በማጥፋት ከመርሁ ተገዥነት እራሱን ሊያገል ይችላል
  • ራይድ አፕልኬሽኑን ሲያቋርጥ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ያስከትላል፡-
    • አገልግሎት ሰጪው በሲስተሙ ላይ ቀሪ ሒሳብ ካለዉ ተመላሽ አይሆንም፣
    • አገልግሎት ሰጪው ውሉ ከተቋረጠ በኋላ ተመልሶ አገልግሎት መስጠት ቢፈልግ ከዚህ በፊት የቀረበት ባላንስ ካለ መጀመርያ ማወራረድ ይኖርበታል
  • ስለ ቅጣት፡- ከዚህ በላይ አፕልኬሽኑን ስለማቋረጥ የተጠቀሰው እና በተለያዩ የትራፊክ ደንቦች እና ህግጋት የተጠቀሱት እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው – አገልግሎት ሰጪው የመኪናው ባለቤትም ይሁን በእርሱ ስር ተቀጥሮ የሚሰራ አሽከርካሪ ከሆነና ከአቅራቢው የፅሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ ለሚሰጠው አገልገሎት ከጥሪ አገልግሎት አቅራቢው የተሰጠውን የጥሪ አገልገሎት መጠቀሚያ የግል አካውንቱን እንዲሁም በራይድ የተመዘገበ ሲም ካርድን ለሌላ ሰው እንዲገለገልበት ሰጥቶ ከተገኘ ወይም ይህንን ቴክኖሎጂ የታርጋ ቁጥሩ በራይድ ባልተመዘገበ መኪና ላይ ሲጠቀም ከተገኘ ለአገልግሎት አቅራቢው የሚከተለውን ቅጣት ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
    • አገልግሎት ሰጪው ይህንን ድርጊት ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈጸመ ለቴክኖሎጂ አቅራቢው ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) የመክፈል ግዴታ አለበት፤አገልግሎት ሰጪው ይህንን ድርጊት ለሁለተኛ ጊዜ ሲፈጽም ከተገኘ ለቴክኖሎጂ አቅራቢው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የመክፈል ግዴታ አለበት፤አገልግሎት ሰጪው ይህንን ድርጊት ከሁለት ግዜ በላይ ሲፈጽም ከተገኘ የቴክኖሎጂ አቅራቢው አሽከርካሪውን ሙሉ ለሙሉ ከሲስተም በማስወጣት የሚሰርዘው ይሆናል፡፡

ልዩ ድንጋጌ

አሽከርካሪው በተላያዩ ጊዚያት ከራይድ የሚላኩ  የተለያዩ ደብዳቤዎች፣ መልዕክቶች፣ የሚሰጡ መግለጫዎች እንዲሁም ራይድ በሚጠራው ስብሰባ ላይ የሚተላለፉ የውሳኔ ሃሳቦች፣ ራይድ የሚያወጣው የአሰራር ፖሊሲ መመሪያ በ 8202 የሚላክ የአጭር መልዕክቶች እና የመሳሰሉት የዚህ መርህ አካል እንዲሆን በሙሉ ፈቃዱ ተስማምተዋል፡፡

ከዚህ በፊት አሽከርካሪው ከራይድ ጋር በወረቀት ስምምነት ገብቶ ከተገኘ እና ውል ለማቋረጥ ከፈለገ በቅርንጫፍ ቢሮ በአካል በመገኘት በደብዳቤ ማቋረጥ ይችላል:: ይህንን ባደረገ ግዜ እና አፕልኬሽኑን ከስልኩ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋ ግዜ ከራይድ ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንዳቋረጠ ይወሰዳል::

Share:

More Posts

2016 E.C. New Year Message from our CEO

የራይድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት:-

እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: መጭው ዓመት በሃገራችን የሰላም- የፍቅር እና የበረከት አመት እንዲሆን በመላው የራይድ ቤተሰብ ስም እየተመኘው- ቤተሰባዊ ወዳጅነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም በቀናነት የምንተሳሰብበት ዘመን እንሚሆን እምነቴ ነው:: ራይድ የሁላችንም ነው! ስለሆነም- በመጭው ዓመት አገልግሎታችንን ሙሉ ለሙሉ ሰው ተኮር በማድረግ በአለም ተወዳዳሪ የሆነና የአፍሪካ ኩራት የሆነ ጠንካራ ድርጅት በጋራ እንደምንገነባ እተማመናለሁ:: መልካም በዓል ከእነቤተሰብዎ እመኛለሁ::

Send Us A Message

Scroll to Top