በባንክ ካርድ የታዘዘ ስራ ሲቀበሉ በዚህ አሰራር መልኩ ይከፈላሉ:-
- ተሳፋሪዎች አፕልኬሽን ላይ በሚገኝ የVisa, Mastercard, Discoverና American Express አማራጮች ክፍያ ሊፈፀም ይችላል:: ለምሳሌ:- ተሳፋሪው ለመክፈል የሚፈልገው አፕልኬሽኑ ውስጥ ባስገባው የባንክ ካርድ ከሆነ ስራ ሰርተው ሲጨርሱ የአሽከርካሪ ክሬዲት ላይ የጉዞው ክፍያ ወዲያው ይገባል:: ያስተውሉ! ክፍያው መጨረሻ ላይ ሲያደርጉ ወደክሬዲትዎ ካልገባ ከተሳፋሪው ጋር ሳይለያዩ ወዲያው ወደ 8812 ደውለው ያሳውቁ::
- ማንኛውም በባንክ ካርድ የተሰራ ስራ ወደ አሽከርካሪ ባላንስዎ ወይም ሬዲትዎ ውስጥ ከገባ በሁዋላ ምንም ካልተጠቀሙበት ሁልግዜ በሳምንቱ መጨረሻ ከአሽከርካሪ ክሬዲትዎ ተቀንሶ Cashout እንዲያደርጉት ወደ RIDE Plus ሲስተሙ automatically የሚያስገባው ይሆናል:: ስለዚህ በሳምንት መጨረሻ የአሽከርካሪ ባላንስዎ ከቀነሰ ሳይደናገጡ ወደ RIDE Plus ሄደው ባላንሱን ሊያገኙት ይችላሉ:: RIDE Plus ላይ የሚገባልዎን ባላንስ ከፈለጉ ወደ Enat Bank ወይም ወደ Telebirr በቅፅበት ማስተላለፍ ይችላሉ