Offense Penalty Sheet

የአፈፃፀም መመሪያ

  1. የራይድ አስፈፃሚ አካል ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ቅጣት ይተገብራል
  2. ተቀጭ ስለጥፋቱ SMS ይደርሰዋል
  3. እገዳ ካልተጣለ በቀር የተጠቀሰውን የጥፋት ይዘት ካገባደደ በኋላ ተቀጭ ወደ ራይድ ሸገር መስሪያ ቤት በመሄድ የጥፋት ቅፅ ሞልቶ ወደስራ ይመለሳል
  4. ተቀጭ ይግባኝ ካለው በፅሁፍ ለራይድ መስሪያ ቤት ማቅረብ ይችላል:: ማንኛውም የቅጣት ይዘት በስልክ ምላሽ አያገኝም

ማሳሰቢያ

  • እንደ ጥፋቱ መደረራረብ አይነት የቅጣት ቀናት ሊደመሩ ይችላሉ
  • አግባብነት ባለው መልኩ በፅሁፍ የሚመጡ የቅጣት ቅሬታዎች ይስተናገዳሉ
  • ይህ የቅጣት መመሪያ በኢ. ፌ. ድ. ሪ. አገራዊ ህጎች ስር ተፈፃሚ ይሆናል
  • መጥፎ የስራ ሬከርድ ራይድ ለወደፊት ከሚሰጠው ጥቅሞች ሊገታ ይችላል:: ስለዚህ እያንዳንዱ አባል አሽከርካሪ መመሪያን ተከትሎ በጥንቃቄ እንዲሰራ ይመከራል
  • የመቅጫ አንቀፆቹ በማንኛውም ግዜ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ ይችላሉ:: ማሻሻያ ሲደረግ ራይድ ለአባላቶች በSMS የሚያሳውቅ ይሆናል

የአሽከርካሪዎች ጥፋት መቀጫ መመሪያ

.ቁ. የጥፋት ዝርዝር ቅጣት
1 የቀጠሮ ስራ ተቀብሎ መሰረዝ በካንስሌሽን ፖሊሲ አንቀፅ መሠረት ያስጠይቃል
2 ከስራ ውጭ ሲሆኑ የአሽከርካሪውን አፕልኬሽን Busy ወይም Offline ላይ አለማኖር (2-3 ግዜ በላይ በተደጋጋሚ ያለምክንያት ስራ ተልኮልዎት ካልተቀበሉ) (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 24 ስዓት የአገልግሎት መቋርጥ

3 የተላከን ስራ ሰርዞ ከተሳፋሪ ጋር በግል የዋጋ ድርድር ማድረግ (የቴክኒካል ብልሽት ካጋጠመ ወዲያው በ8294 ማሳወቅ ግዴታ ነው) (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 2 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)

በተጨማሪም የዋጋውን ጭማሪ ልዩነት ከአሽከርካሪው ክሬዲት ላይ ይቀነሳል

4 ሜትር ከቆጠረው በላይ ስልክን ለተሳፋሪ ሳያሳዩ ተጨማሪ ዋጋ ማስከፈል (ተሳፋሪ በአፕልኬሽን ተጠቅሞ ኩፖን ካስገባ Confirm ሲጫኑ ከዋጋው አንስቶ ወደ እርስዎ Credit ስለሚጨምር ያስተውሉ) (መጀመሪያ ግዜ) 2 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

(2 ግዜ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)

በተጨማሪም የዋጋውን ጭማሪ ልዩነት ከአሽከርካሪው ክሬዲት ላይ ይቀነሳል

5 ምንም ስራ ሳይሰሩ ከ1 ወር በላይ የራይድን ቢሮ ሳያሳውቁ መቆየት ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)
6 ተሳፋሪን ማጉላላትመሳደብማመናጨቅማጥላላትማስፈራራትማንቋሸሽ:: የተሳፋሪው ቅሬታ በ8294 ተቀርፆ ይቀመጣል:: አሽከርካሪው ስለተፈጠረው ሁኔታ ለራይድ ቢሮ ወዲያው ማሳወቅና ቅሬታውን መፍታት ይኖርበታል:: በተሳፋሪና በአሽከርካሪ መሃከል የሚፈጠር ማንኛውም አለመግባባት ወደ 8294 መመራት ይኖርበታል (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)

7 ተሳፋሪን ሳያስፈቅዱ ረዥም መንገድ ወውሰድ (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 24 ስዓት የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

በተጨማሪም የዋጋውን ጭማሪ ልዩነት ከአሽከርካሪው ክሬዲት ላይ ይቀነሳል

8 የራይድ አፕልኬሽንዎን ሌላ ሰው እንዲሰራበት አሳልፎ መስጠት (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 3 ቀን የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) 1 ወር የአገልግሎት መቋርጥ

9 የራይድን ሰራተኞች መሳደብማመናጨቅማጥላላትማንቋሸሽማስፈራራት (መጀመሪያ ግዜ) 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

(2 ግዜ) 1 ወር የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)

10 ስርቆት ወይም መኪና ውስጥ የጠፋን እቃ በወቅቱ አለመመለስ (ተጣርቶ ከተገኘ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)
11 ምንም አይነት የአልኮሆል መጠጥ፣ በየትኛውም መጠን ጠጥቶ ተሳፋሪን ማጓጓዝ (መጀመሪያ ግዜ) 1 ወር የአገልግሎት መቋርጥ

(2 ግዜ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)

12 አሽከርካሪው በማንኛውም ግዜ ጫት መኪና ውስጥ ይዞ መገኘት (መጀመሪያ ግዜ) 2 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

(2 ግዜ) 1 ወር የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) ላልተወሰነ ግዜ ከስራ እገዳ (የከፈሉት ባላንስ ዜሮ ይሆናል)

13 የመኪናን ውስጥና ውጭ በንፅህና አለመያዝ ፤ መጥፎ የግል ጠረንን አለማስወገድ ፤ አግባብነት ያለው ባለመሉ እጅጌ ሸሚዝ ፣ሹራብ ወይም ቲሸርት አለማድረግ፤ ሙሉ ሱሪ ከሽፍን ጫማ ጋር ለብሶ አለመገኘት (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

 

14 በአንድ ቀን ውስጥ የአስቸኳይ ስራ በተደጋጋሚ እየተቀበሉ መሰረዝ (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 24 ስዓት የአገልግሎት መቋርጥ

15 ከተሳፋሪ ጋር ስለኮሚሽን ክፍያና የውስጣዊ አሰራር ቅሬታዎች ማንፀባረቅ ወይም መወያየት 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ
16 በተጠየቀ ግዜ የወረቀት ሪሲት ለተሳፋሪ ወዲያው አለመስጠት (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ ወይም አሽከርካሪው ሪሲቱን ሰቶ ለራይድ ቢሮ መረጃ ካቀረበ ወደስራ ይመለሳል

17 የተሳሳተ ወይም የሃሰት ሪሲት ለተሳፋሪ ወይም ለራይድ ድርጅት መስጠት 2 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ
18 መኪና ውስጥ ማጨስ ወይም የሲጋራ ሽታ መኖር (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 1 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

(3 ግዜ) 2 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

19 የራይድ አፕልኬሽን የተጫነበትን ስልክ ጉዞ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሳፋሪ ሂሳብ በሚታይበት መልኩ ፊት ለፊት አለማኖር (መጀመሪያ ግዜ) የቃል ማስጠንቀቂያ

(2 ግዜ) 24 ስዓት የአገልግሎት መቋርጥ

20 በሌሎች አንቀፆች ከተገለፀው ውጭ ማንኛውንም አይነት የሂሳብ ማጭበርበር ማድረግ 2 ሳምንት የአገልግሎት መቋርጥ

በተጨማሪም የዋጋውን ጭማሪ ልዩነት ከአሽከርካሪው ክሬዲት ላይ ይቀነሳል

21 በምዝገባ ወቅት የተፈረመውን የአሽከርካሪዎች ውል በሙሉም ሆነ በከፊል መጣስ እንደጥፋቱ ክብደትና ቅለት በራይድ ቢሮ ከፍተኛ ሃላፊዎች የሚወሰን ይሆናል

Share:

More Posts

RIDE ከOVID ጋር በጋራ ለአሽከርካሪዎች ቤቶች ሊገነባ ነው

ኦቪድ ሪል እስቴት እና ራይድ ትራንስፖርት (Hybrid Designs PLC) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስራ ውልስምምነት ተፈራረሙ፡፡  መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ. ም አዲስ አበባ ኦቪድ ሪል እስቴት በኢትዮጵያ በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ

2016 E.C. New Year Message from our CEO

የራይድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት:-

እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: መጭው ዓመት በሃገራችን የሰላም- የፍቅር እና የበረከት አመት እንዲሆን በመላው የራይድ ቤተሰብ ስም እየተመኘው- ቤተሰባዊ ወዳጅነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም በቀናነት የምንተሳሰብበት ዘመን እንሚሆን እምነቴ ነው:: ራይድ የሁላችንም ነው! ስለሆነም- በመጭው ዓመት አገልግሎታችንን ሙሉ ለሙሉ ሰው ተኮር በማድረግ በአለም ተወዳዳሪ የሆነና የአፍሪካ ኩራት የሆነ ጠንካራ ድርጅት በጋራ እንደምንገነባ እተማመናለሁ:: መልካም በዓል ከእነቤተሰብዎ እመኛለሁ::

RIDE Company Profile

Hybrid Designs PLC is a revolutionary Mobility technology company that aspires to implement simple, practical, and efficient mobility systems in Africa. Our

Send Us A Message

Scroll to Top