RIDE ከOVID ጋር በጋራ ለአሽከርካሪዎች ቤቶች ሊገነባ ነው

ኦቪድ ሪል እስቴት እና ራይድ ትራንስፖርት (Hybrid Designs PLC) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስራ ውልስምምነት ተፈራረሙ፡፡ 

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ

አዲስ አበባ

ኦቪድ ሪል እስቴት በኢትዮጵያ በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ያለ ሪል እስቴት ሲሆን፤ ለአብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ጥራት ያላቸውን ቤቶች ገንብቶ ገቢን ባገናዘበ መልኩበተመጣጣኝ ዋጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ አንቱታን አግኝቷል፡፡ አሁንም በርካታ ቤቶችን በመገንባት ላይ ትኩረቱንአድርጎ እየሰራ ይገኛል። 

የኦቪድ ግሩፕ አካል የሆነው ኦቪድ ሪል እስቴት ለግንባታ የሚጠቀምባቸውን ግብአቶች ከእህት ኩባኒያዎቹ መረከቡ እና የአልሙኒየም ፎርም ወርክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀሙ የግንባታን ጊዜ እና ወጪ በእጅጉ በመቀነሱ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች ለገበያ ማቅረብ አስችሎታል። ከዚህ ቀደም የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደርን ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በ18 ወራት ገንብቶ ያስረከበ ሲሆን፣ በተጨማሪም በልደታ፣ በሪቼ፣ በአዋሬ እንዲሁም በባህር ዳር ከተማ በርካታ ቤቶችን ገንብቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስረክቧል። 

ኦቪድ ሪል እስቴት  ሁልጊዜም ለቃሉ ታማኝ በመሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች ቤቶችን ማስረከብ መርሁ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ይህንንም ለማስቻል ጠንካራ የሆነ አመራር በማዋቀር እና ጠንካራ የስራ ባህልን በሰራተኞቹ መካከል በመገንባት ቀን እና ሌሊት የሚተጋ ድርጅት ነው። 

በአሁን ሰዓት የጫካ የቤቶች ፕሮጀክት፣ የኪንግስ ታወር ፕሮጀክትን እንዲሁም የኦቪድ ቦሌ ቡልቡላ ከተማ ፕሮጀክትን ይዞ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በኦቪድ ቦሌ ቡልቡላ ከተማ ፕሮጀክት ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የገቢያ ማዕከሎችን የያዘ ከ60,000 በላይ መኖሪያ ቤቶች ያሉት የማህበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበዘመናዊ ከተማ በመገንባት ላይ ይገኛል። ይህንንም አላማውን ለማሳካት ኦቪድ ሪል እስቴት ከተለያዩ ጠንካራ ተቋማት ጋር በአጋርነት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 

በሌላ በኩል ለደንበኞቹ እና ለአሽከርካሪዎቹ ልዩ ትኩረት ሰጥቶእየሰራ የሚገኘው ራይድ ትራንስፖርት የአግልግሎት አድማሱንበየዘርፉ በማስፋት በHybrid Designs PLC ስር ከሚገኙ እህት ኩባንያዎቹ ጋር በጋራ በመሆን ደንበኞቹን፣አሽከርካሪዎችን እንዲሁም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ስር የሚገኙ የጥበብ ባለሙያዎችን የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ሲሰራ ቆይቷል።

የመኖሪያ ቤት እጦት የበርከታ ነዋሪዎች ችግር መሆኑንበመገንዘብም ለችግሩ የጋራ መፍትሄ ለመፈለግ የሚያስችሉጥናቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያከናውን ቆይቷል፡፡  በተለይም በከተማችን በአዲስ አበባ ችግሩ ጎለቶ የሚታይ ሲሆን ለዚህ መሰረታዊ እና አንገብጋቢ ጉዳይ በጋራ መፍትሄ ለማበጀት ተባብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን በማመን ከኦቪድ ሪል እስቴትጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ 

የስምምነቱ አጠቃላይ ዓላማ ኦቪድ ሪል እስቴት በHybrid Designs PLC ስር ለሚገኙ ተቋማት የራይድ ቤተሰቦች የመኖሪያቤት ሽያጭ የዋጋ ቅናሽ አሰራርን አሰራርን በማመቻቸት የቤትባለቤት ለመድረግና በአጠቃላይ የራይድ ቪሌጅ (የራይድመንደር) ለመገንባት ሲሆን ሀይብሪድ እና በስሩ ያሉ ተቋማታምኦቪድ ሪል እስቴት ለሚያቀርባቸው የመኖሪያ ቤት ሽያጭአገልግሎቶች የገበያ እንቅስቃሴዎችን በማከናወንየማስተዋወቅ ስራዎችን ከሌሎች እህት ተቋማቱ ጋር በጋራበትስስር ለመስራ ተስማመተዋል፡፡ የስምምነቱን የተወሰኑነጥቦችን በዝርዝር ስንመለከት ፡-

• ኦቪድ ሪል እስቴት ለራይድ ትራንስፖርት፣ በስሩ ለሚገኙ እህትተቋማት እና ራይድ ቤተሰብ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችንበተመጣጣኝ የዋጋ ቅናሽ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆንበአጠቃላይ RIDE VILLAGE (የራይድ መንደር) ለመገንባትአስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፡፡

• ሀይብሪድ ዲዛይንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ራይድኦቪድ ሪልእስቴት ለአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለሚገኙ ደንበኞቹለሚያቀርበው የቤት ሽያጭ አገልግሎት የገበያ ንቅናቄውንበማስተዋወቅ ይስራል፣ ያሰተባብራል፡፡ 

• የራይድ ትራንስፖርት አሽከርከሪዎች ኦቪድ ሪል እስቴትለሽያጭ ያዘጋጃቸውን ቤቶች በተሸከርካሪዎቻቸው እናበሌሎች የራሱ ፕላትፎርሞች የማስተዋወቅ ስራ ይሰራሉ፡፡

• በሰዋሰው መልቲ ሚዲያ በኩል የሚገኙ አንጋፋና ወጣትየጥበብ ባለሙያዎች፣አርቲስቶች እና ከያኒያንን በማስተባበርኦቪድ ሪል እስቴት የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶችን እናየቤት ሽያጭ ንቅናቄዎችን ያከናውናል፡፡

• ሀይብሪድ ዲዛይንስ በቴክኖሎጂ የታገዙ የተለያዩፕላትፎርሞችን በመጠቀም የኦቪድን ምርትና አገልግሎትማስተዋወቅ እና የኦቪድ ሪል እስቴትን  የሚመለከቱ የምክክርፎረሞችን በሚዲያ ያዘጋጃል፣

• በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት ከላይ ለተጠቀሱት የራይድቤተሰቦች ምቹ እና ዘመናዊ መንደርን በመገንባትናበቴክሎጂ ትስስር የራይድ ቤተሰቦችን ህይወት ቀላልበማደርግ ረገድ የበኩላቸውን  አስተዋፅኦ ለማበርከት በትጋትየሚሰሩ ይሆናል፡፡ 

በአጠቃላይ ራይድ ትራንስፖርት ላለፉት ዓመታት ቁልፍ የሆኑስኬቶችን ማሳካት የቻለ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ፡-

• ዲጂታይዜሽን እቅዳችንን በተጠና መልኩ የተገበርንበት ፣ 

• የአሽከርካሪዎቻችንን እና የደንበኞቻችንን ደህንነት ከህግአስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር በተሟላ መልኩ በስኬትያስጠበቅንበት እንዲሁም አደጋን የተከላከልንበት፣ 

• የደንበኛን ምቾትና የአገልግሎታችንን ጥራት የሚያሳድጉየተለያዩ ወሳኝ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን እናአሰራሮችን በስኬት የከወንበት እና የGreen Initiative አካልየሆነውን Electric Vehicle አቅጣጫችንን ያሰመርንበት፣ 

• አጋር የRIDE አሽከርካሪዎች ጋር በስኬት ተናበን አለምአቀፋዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ቀናነት የተሞላበትCustomer Service የሰጠንበት ፣

• ትልቅ መሰረት የሚጥሉ ድርጅት ለድርጅት ግንኙነቶችንየመሰረትንበት እንዲሁም ፣

• ድርጅታችን በቀዳሚነት በሃገራችን ያስጀመረውየኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ደረጃውን በጠበቀመልኩ በዲጂታል ስርአት ግብር እንዲከፍል ከባለድርሻአካላት ጋር በጥምረት የሰራበት ውጤታማ ግዜ ነበር::

Share:

More Posts

2016 E.C. New Year Message from our CEO

የራይድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት:-

እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: መጭው ዓመት በሃገራችን የሰላም- የፍቅር እና የበረከት አመት እንዲሆን በመላው የራይድ ቤተሰብ ስም እየተመኘው- ቤተሰባዊ ወዳጅነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም በቀናነት የምንተሳሰብበት ዘመን እንሚሆን እምነቴ ነው:: ራይድ የሁላችንም ነው! ስለሆነም- በመጭው ዓመት አገልግሎታችንን ሙሉ ለሙሉ ሰው ተኮር በማድረግ በአለም ተወዳዳሪ የሆነና የአፍሪካ ኩራት የሆነ ጠንካራ ድርጅት በጋራ እንደምንገነባ እተማመናለሁ:: መልካም በዓል ከእነቤተሰብዎ እመኛለሁ::

RIDE Company Profile

Hybrid Designs PLC is a revolutionary Mobility technology company that aspires to implement simple, practical, and efficient mobility systems in Africa. Our

Send Us A Message

Scroll to Top