ውድ የራይድ ቤተሰብ ከስማችን በላይ የእርስዎ ደህንነት ያስጨንቀናል:: የራይድ አሽከርካሪ ማለት የከተማችን አምባሳደር፣ ሃላፊነት የሚሰማው የቤተሰብ አስተዳዳሪ ሲሆን ከተማችንን ሳይታክት 24 ሰዓት የሚያገለግል እንቁ ዜጋ ነው:: ስለሆነም ሁሉም አባላት እነዚህን አጭር ተግባራት በመከወን ተቀናጅተን የጋራ ደህንነታችንን በማስጠበቅ ተባብረን ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ የስራ ሁኔታ እንድንፈጥር እገዛዎትን እንሻለን:-
ሁልግዜ በስራ ወቅት የመኪናዎ በር መቆለፉን አይዘንጉ:: ከተቻለ ማርሽ ሲገባ automatically እንዲቆልፍ ቢያደርጉ ይመከራል
- ተሳፋሪ እንዳይዘረፍ ያግዛል
- እርስዎም ሳያዩት ስልክዎ እንዳይዘረፍ ያግዛል
- በምሽት ማንኛውም አይነት ጥቃት እንዳይደርስብዎ ይከላከላል
- ህፃናት መኪና ውስጥ ካሉ አደጋ እንዳይደርስ ይከላከላል
ሁልግዜ መንገድ ላይ ተሳፋሪን ሲያነሱ RIDE Plusን በመጠቀም ሜትር ያስጀምሩ::
የRIDE Plus ሜትር ውስጥ የተሳፋሪውን ስልክ ቁጥር ሲያስገቡ ማንነቱን መመልከት የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም የማይታወቅ ተሳፋሪ ከሆነ ፎቶ እንዲያስገቡ ይጠይቃል:: በዚህም መሰረት ሁልግዜ ተሳፋሪ መንገድ ላይ ሲያስቆምዎ እነዚህን ተግባራት በጥንቃቄ ይከተሉ
i. ተሳፋሪ ከመግባቱ በፊት በሩን ሳይከፍቱ ስልክ ቁጥር ተቀብለው RIDE Plus Street Pickup ውስጥ ያስገቡ
ii. የተሳፋሪው መረጃ ወይም ፎቶ ሲስተም ላይ ከመጣ አስተያይተው ተሳፋሪን ለማስገባት በር ይክፈቱ:: ካልሆነ ተሳፋሪው ውጭ እንዳለ ፎቶ ያንሱ:: በፍፁም ተሳፋሪን ሳያስተያዩ ወይም ፎቶ ሳያነሱ ወደመኪናዎ ውስጥ አያስገቡ
በምሽት ተሳፋሪን ሲያነሱም ሆነ ሲያደርሱ ሰው ያለበት አካባቢ መሆኑንና በቂ መብራት ያለበት ቦታ መሆኑን ያረጋግጡ
በብዛት ዝርፊያዎች የሚፈፀሙት ጨለማን ተገን በማድረው ወይም ተመልካች በሌለበት እንደመሆኑ መጠን ሁልግዜ ሰው ባለበት እንዲጭኑ ወይም እንዲያወርዱ ይመከራል:: በተጨማሪም ውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በምሽት ከመጠቀም ተሳፋሪን አግባብተው በዋናው መንገድ እንዲሄዱ ይመከራል::
ምናልባት ተሳፋሪን ይዘው ጨለማ መንገድ ውስጥ መግባት ቢያስፈልግ ዎ ጥሪ ማዕከል ደውለው አጋዥ አሽከርካሪ እንዲላክልዎ ይጠይቁ
ያስተውሉ! ማንኛውም ዘራፊ ለራሱ የሚመችን አጋጣሚ እንጂ እርስዎን የሚጠብቅ መንገድና ስልት አይቀይስም
በምሽት ወደውስጥ መንገድ እንዲገቡ ከተገደዱ በጋራ የተሳፋሪን ደህን ነት ለመጠበቅ ሲባል ይህንን መንገድ ይጠቀሙ
ለጋራ ደህንነት ተሳፋሪን በበቂ ሁኔታ አስረድተው በጥሪ ማዕከል ይደውሉና አጋዥ ተከታይ አሽከርካሪ እንዲላክልዎ ይጠይቁ:: አጋዥ ሲጠሩ የሚጠብቁበት ቦታ መብራት ያለበትና ሰው የተሰባሰበበት እንዲሆን ይመከራል::
መጀመሪያ እራስ ደህና የሚለውን መርህ ይከተሉ:: ስለት ወይንም መሳሪያ ከያዘ ዘራፊ ጋር በምንም መልኩ አይታገሉ ::
ዝርፊያ በደርስብዎ ህግ ስራውን እንዲሰራ እድል ይስጡ:: ይዘገይ እንደሆን እንጂ ወንጀለኛ መያዙ አይቀርም:: በመሆኑም ለሚያልፍ ነገር የራስዎን ደህንነት በምንም መልኩ አሳልፈው አይስጡ::
ማንኛውም አይነት ችግር ቢገጥምዎ በፍጥነት በ991 ለፖሊስ ይደውሉ:: ቀጥሎ በ8812 ለጥሪ ማዕከላችን ያሳውቁ:: የህግ እገዛ ለማድረግ ድርጅታችን ምንግዜም ዝግጁ ነው!