RIDE ከእናት ባንክ ጋር በመተባበር ቅንጡና ዘመናዊ መኪኖች የፋይናንስ ብድር ያመቻቸ ሲሆን በዛሬው እለት መኪኖቹን አስመርቆ ወደስራ አስገብቷል::
ከዚህ ቀደም እናት ባንክ ለራይድ አሽከርካሪዎች ባዘጋጀው ብድር መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ግብራቸውን በወቅቱ ለመክፈል ፣ አደጋ ሲገጥማቸው ጥገና ለማከናወን እንዲሁም ማንኛውም ማህበራዊ ችግር ሲገጥማቸው እክላቸውን በፍጥነት ለመፍታት እንደ እናት አለኝታነቱን ያሳየ ሲሆን ፣ አሁን ደግሞ ትጉህ የራይድ ቤተሰብ አባላት የ2022 ሞዴል ዘመናዊ መኪና ባለቤት እንዲሆኑ በተግባር እየሰራ ይገኛል::
ዛሬ ነሃሴ 19/2014 ዓም ዝግጅት ላይ የእናት ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ እንደተናገሩት ባንካቸው በቀጣይነት ይህንን እድል አስፍቶ ተግተው የሚሰሩ የራይድ አሽከርካሪዎችን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ፣ እንደቤት የመሳሰሉ የብድር አይነቶችንም ለማካተት እቅድ መያዙን ጠቅሰዋል:: የራይድ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ ለራይድ ቤተሰብ አባላት ባስተላለፉት መልዕክት በቀጣይ የአጭር ግዜ አነስተኛ መጠን ብድርም ሆነ የረጅም ግዜ ትልቅ መጠን የብድር አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ በእናት ባንክ ፈጥነው አካውንት ከፍተው ቁጠባ እንዲጀምሩ አስገንዝበዋል:: በዝግጅቱም በዛሬው የብድር አገልግሎት መኪና ያገኙ አባላት ደስታቸውን የገለፁ ሲሆን ሌሎች አባላትም ከራይድና ከእናት ባንክ ጋር እየሰሩ የሚመጡ እድሎችን እንዲጠቀሙ በአፅኖት አሳስበዋል።