ከተሳፋሪ አፕልኬሽን ትዕዛዝ ሲደርስዎ የተሳፋሪውን መገኛ ቦታ በቡርትካናማ የሰው ምልክት ካርታዎ ላይ ይቀመጣል። ይህ ቦታ ተሳፋሪው የያዘውን ስልክ መገኛ ያመላክታል
የእለት ተእለት ሂሳብ ዝርዝርዎን ለመመልከት ይህንን ይከተሉ : Menu > Credit > Transaction History
ተራ ቁጥር ትንተና
- Online/Offline – ሁልግዜ ወደስራ ሲገቡ ብቻ Online ያድርጉ። ሲጨርሱ ደግሞ Offline ያድርጉ። ያስተውሉ፦ offline አድርገው online ሲያደርጉ ሁልግዜ ከተራ መጨረሻ ሁነው ስራ ይጀምራሉ
- SOS – በአደጋ ግዜ ወዲያው ለመደወል የአደጋ ግዜ ተጠሪዎን ፕሮፋይልዎ ውስጥ ያስገቡ። ቁጥሩን ለማስገባት Menu >> press your pic to enter Profile >> Profile Information >> Emergency Contact
- Work Zone – የስራ ክልልዎን ይሙሉ። በምን ያህል ርቀት ውስጥ ስራ እንደሚገባልዎ መሙላት ይችላሉ። ያስታውሱ፦ ሲስተሙ ስራ የሚልከው በወፍ በረር ርቀት ነው
- Work Heat Map – ይህ መጠቀሚያ የስራ ፍሰትን ይጠቁማል። ስለአጠቃቀሙ በዝርዝር ከስር ይመልከቱ
- Traffic Indicator – ይህ መጠቀሚያ የትራፊክ ሁኔታን በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን፣ በዝርዝር ስለአጠቃቀሙ ከስር ይመልከቱ
በአካባቢ ያለን የትራፊክ ሁኔታ በቀጥታ (Live) ለመፈተሽ የትራፊክ መብራት ምልክቷን መጫን ይቻላል። ከላይ በካርታው ላይ እንደሚመለከቱት የትራፊክ መስመሮች ከአረንጓዴ እስከ ደማቅ ቀይ ድረስ በየደረጃው ተቀምጠዋል። አረንጓዴ ትራፊክ መስመር ጭንቅንቅ የሌለበትን ቦታ የሚያሳይ ሲሆን፣ ወደ ደማቅ ቀይ እየተጠጋ ሲመጣ መጨናነቅን ያሳያል። ለጉዞ ዝግጁ ሲሆኑ የሚመርጡት አቅጣጫ ስንት ደቂቃ እንደሚፈጅና ርቀቱን ያሳያሉ። በተለይም የትራፊክ መዘጋጋት የሚያሳዩ ቀያ መስመሮች ለምን ያህል ግዜ ትራፊኩን እንደሚያዘገዩት ያመላክታሉ።