Enat bank has partnered with RIDE to provide a short and long term loans to drivers. Here are the terms:-
- እናት ራዕይ: ይህ ብድር የተዘጋጀው ለራይድ ባለ ራዕይ አሽከርካሪዎች ሲሆን ብድሩም ለአዲስ መኪና መግዣ የሚውል ይሆናል። ከታሰበው የመኪና ዋጋ ውስጥ ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን በስድስት ወር ውስጥ ከቆጠቡ የራይድ አባል አሽከርካሪዎች በአምስት ዓመት ተከፋይ በሚሆን በአስራአራት በመቶ ወለድ ብቻ ላሰቡት መኪና እስከ ሰባ በመቶ የሚሆን ብድር ከአናት ባንክ ማግኘት ይችላሉ።
- እናት እፎይታ: ይህ ብድር የተዘጋጀው የራይድ አሽከርካሪዎች በስራ ላይ እያሉ ለሚግጥማቸው ለመኪና ጥገና ለአመታዊ ግብር ክፍያ ብሎም ተያያዝ ወጪዎች ለመሸፈን የሚውል ነው። ከአስር እስከ አስራአምስት በመቶ በሚታሰብ አመታዊ ወለድ እስከ 10,000ብር ብድር ማገኘት ይችላሉ።
- እናት ደራሽ: ይህ ብድር የተዘጋጀው ለራይድ አሽከርካሪዎች ስራ ማስኬጃ ማለትም ለራይድ ኮሚሽን እንዲውል ነው። ይህ ብድር ምንም አይነት ወለድ አይታሰብበትም።
For More info Call these numbers 0114701440 / 0116695942 / 0114708367 / 0115589416