Ethiopia's Pride

የአሽከርካሪዎች የስራ መመሪያ

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት መለኪያ

በራይድ ቤተሰብ ውስጥ ታቅፈን ስንሰራ የጋራ ገፅታችንን በራሳችን ተነሳሽነት መገንባት እንደሚጠበቅብን ያልተፃፈ ቃለ መሀላ ነው። ተደጋግፈን የምናመጣው የጋራ ገፅታ የአገልግሎውስጥታችንን ህልውና ከማስጠበቅም አልፎ መዋቅራችንን ወደላቀ ደረጃ እንድናሸጋግር ቀና የሆነ መንገድ ይከፍትልናል። በመሆኑም ሁሉም አባል አሽከርካሪ የሚከተሉትን የጥራት መመዘኛ ነጥቦች በቀናነት እንደሚተገብር ይጠበቃል።

  1. በሚገባ የተጠገነ ደህንነቱ የተጠበቀ ንፁህ መኪና ማቅረብ
  2. ከ10 ደቂቃ ባነሰ ግዜ ውስጥ ተሳፋሪን ማንሳት
  3. የደንበኛን ምቾት የጠበቀ ቀና መስተንግዶ መስጠት
  1. በሚገባ የተጠገነ ደህንነቱ የተጠበቀ ንፁህ መኪና ማቅረብ – መኪናዎን ቢያንስ በሁለት ወር አንዴ በፕሮግራም ማስፈተሽ በኋላ ሊመጣ ከሚችል ያልተጠበቀ ወጪ ሊያድንዎ ይችላል። እንደሚያውቁት መኪና አላቂ ንብረት ነው። ምናልባት ይህንን ሀቅ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በየመንገዱ መኪናዬ ይቆም ይሆን እያሉ ከመሳቀቅ፣ ገቢዎን በአግባቡ እያመጣጠኑ የመኪናዎን ኢንቨስትመንት መመለስ እንዲሁም ቤተሰብዎን በአግባቡ መምራት ይችላሉ። ንፅህናን በተመለከተ አንድ ሚስጥር እናካፍልዎ፤ ፅድት ያለ መኪና ውስጥ የተሳፈረ ሰው ከፍተኛ ቲፕ ከመስጠቱ በተጨማሪ አሽከርካሪውን የሚያናግርበት አንደበትም የተለሳለሰ ነው። ስራውን አከብሮ የሚሰራ ሰው ይከበራል፣ ምክንያቱም ጠንቃቃ ሰው እንደሆነ በእይታ የሚገለፅበት መንገድ ነውና።
  2. ከ10 ደቂቃ ባነሰ ግዜ ውስጥ ተሳፋሪን ማንሳት – ”ሲቆይብኝ ሄድኩኝ” የሚለውን የተሳፋሪ ቅሬታ በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ አሽከርካሪው በአጭር ግዜ ውስጥ ተሳፋሪ ጋር እንዲደርስ ይመከራል። ተሳፋሪ ጋር በቶሎ ለመድረስ ከስር በተናጥል የተሰጡትን ተሞክሮዎች ይመልከቱ።
  3. የደንበኛን ምቾት የጠበቀ ቀና መስተንግዶ መስጠት – ሁሉም አባል ከሽከርካሪ ስራ በጀመረ በ 1 ወር ግዜ ውስጥ የአገልግሎት ጥራት ስልጠና እንዲወስድ ይደረጋል። በዚህ ስልጠና ላይ አሽከርካሪው Platinum Rule የተሰኘውን መርህ በጥልቀት ይረዳል። (Platinium Rule: የተሳፋሪን ፍላጎት ተረድቶ እንደሚፈልገው ቀና መስተንግዶ መስጠት)

በዝርዝር ጥሩ ስነምግባር መመሪያችንን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

የጥፋት ዝርዝርና እርምት

መቼስ የሰው ልጅ እንደፈጣሪ ፍፁም አይደለም። ሳያውቅ እንደሚሳሳት እንረዳለን፤ ጥፋቱን አርሞ ጥሩ የቤተሰባችን አባል እንዲሆንም የሁላችንም ፍላጎት ነው። የራይድ አስተዳደር አቅጣጫ አሰራራችንን ከግዜ ወደግዜ እያሻሻልን ፓርትነሮቻችን መብትና ግዴታቸውን በሚገባ እንዲረዱ መንገዶችን ማመቻቸትና ስልጠናዎችን ማሰናዳት ነው።

በጥቅሉ የስነምግባር ጉድለት ማረሚያ ሰነድ እዚህ ሊንክ ላይ ተቀምጧል። ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

የራይድ መገልገያ ስልክ ቴክኒካል መፈተሻ

ምንም አስማት ወይንም ሚስጥር የለውም። የራይድ ሲስተም በአፕም ሆነ በጥሪ ማዕከል ሲታዘዝ ስራ የሚያደላድለው የሚከተሉትን መስፈርቶች ሁሉ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው። አሽከርከካሪው በትክክል ካልተከተላቸው እነዚህ መስፈርቶች የስራ ድርሻ ማበላለጥን ያመጠጣሉ

  • መጀመሪያ ሲስተማችን ስልክዎ በስራ ድልድል ወቅት ምንም የማይቆራረጥ ኔትወርክ እንዳለው ያረጋግጣል። ስራውን ወደ አሽከርካሪዎች ለመመደብ በሚዘጋጅበት ወቅት ስንት መኪኖች ከተሳፋሪው ዙሪያ online ሆነው እየጠበቁ መሆኑን ይቆጥራል። በዚህ ወቅት የስልክ ጥሪ ላይ መሆን፣ ኔትወርክ ለአፍታም ቢሆን ወጣ ገባ የሚልበት ቦታ ላይ መገኘት፣ ስልክዎ ላይ የተጫኑ አፕልኬሽኖች የስልክዎን ኔትወርክ እንዲያጨናንቁ ማድረግ፣ የስልክዎ ፕሮሰሰር ፍጥነት ዝቅተኛ መሆኑ፣ አንድ ሲም ብቻ አለመጠቀምና ዋይፋሪ አብርቶ መተው ከቁጥር ውስጥ እንዳይገቡ እንቅፋት ከሚሆኑ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶች ናቸው። ያስተውሉ፤ ከቁጥር ውስጥ አለመግባት ሲስተሙ በስራ ላይ እንዳልሆኑ ይቆጥርዎታል ማለት ነው።
  • Online የሆኑትን መኪኖች ከቆጠረ በኋላ ቅድሚያ የሚሰጠው መኪና በእነዚህ ነጥቦች ይለያል። በቅርብ ሰዓት ስራ ያልሰራ፣ ስራ ያላዘለለ (ያልሰረዘ) ፣ ከተሳፋሪ የተሻለ መገምገሚያ ኮኮብ ያለው ከምደባው ቀዳሚ ይሆናል። የደረሰው አሽከርካሪ ካልተቀበለው ሲስተማችን እንደ ደረጃው ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ተጠቅሞ እያገናዘበ ያደላድላል።
  • መለማመጃ፦ በተሳፋሪው ዙሪያ 10 online መኪኖች ተገኙ እንበል። 6ቱ ስራ የሰረዙት፣ ያዘለሉት፣ የጨረሱት፣ ስራ ያሳለፉት እንበል ከ 35 ደቂቃ ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ሲሆን 4ቱ ከዛ በላይ online ሁነው ሲጠብቁ ነበር (‘ሀ’ 45 ደቂቃ ጠብቆ ምንም አልሰረዘም፣ አላዘለለም፣ አልሰራም። ‘ለ’ 45 ደቂቃ ጠብቆ አዘልሏል አሳልፏል ወይም ሰርዟል። ‘ሐ’ ከ 50 ደቂቃ በፊት ስራ ጨርሶ፣አዘልሎ፣ ሰርዘዞ ወይም አሳልፎ እየጠበቀ ነበር። ‘መ’ ከ 50 ደቂቃ በፊት ሰስራ ጨርሶ፣ ሰርዞ፣ አሳልፎ እነጠበቀ ነበር ነገር ግን ከ ‘ሐ’ የበለጠ አቬሬጅ ኮኮብ ነጥብ አለው) የራይድ ሲስተም ካወዳደረ በኋላ ስራውን ቅድሚያ ለማን የሚሰጥ ይመስልዎታል? ** መልሱ ከስር ተሰጥቷ

የራይድ አፕ የሚገኝበትን ስልክ ለስራ ዝግጁ ለማድረግ የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲከተሉ ይመከራል። እነዚህ ነጥቦች ካልተተገበሩ የሂሳብ ስህተትን ያበዛሉ፣ ስራ የማግኘት እድልዎን በ70% ይቀንሳሉ፣ እንዲሁም አቅጣጫ በማሳት የስራ ማስተጓጎል ያደርሳሉ።

  1. የስልክዎ ቨርዥን ከ 8.0 በላይ መሆኑንና 3 RAM በላይ መሆኑን ያረጋግጡ። ቨርዥኑን update ሲያደርጉ የቀፎውን ፍጥነት እንደማይቀንሰው ያረጋግጡ። ያስተውሉ፦ አንዳንድ ስልኮች የቅርብ update ቢቀበሉም የስልኩን ፍጥነት የቀንሳሉ
  2. የራይድናgoogle map አፕልኬሽኖች ሁሌ update መደረጋቸውን ያረጋግጡ። ያስተውሉ ሁሌ update የሚለቀቀው በፊት ከተለቀቀው ላይ ስህተትን ለማረም ስለሆነ ከስር ከስር ተከታትለው update ያድርጉ
  3. የስልክዎ setting ውስጥ ይግቡ፦ Date and Time ውስጥ Automatic time zone መብራቱን ያረጋግጡ። Location ውስጥ ገብተው high accuracy ላይ መሞላቱን ያረጋግጡ። በተጨማሪም አንድ ሲም ብቻ በቀፎዎ ውስጥ ይጠቀሙ (ዋይፋይ በፍፁም አያብሩ)
  4. የራይድ ስልክ ቁጥርዎን ወደ ሌላ መደወያ ስልክ forward ያድርጉ። ለተሳፋሪ መደወያ መጠቀም ይችላሉ፣ ሲደወልልዎ ግን ወደሌላ መሄድ አለበት።
  5. እንዳይረሱ፦ የራይድ ስልክ ሁልግዜ የቴሌ ክሬዲት እንዳለው ያረጋግጡ። በተጨማሪም የራይድ ክሬዲትዎን menu>>credits ውስጥ በመግባት ለስራ በቂ ሂሳብ እንደለዎ ያረጋግጡ

ልዩ ልዩ አሰራሮች

  1. የኤርፖርት መግቢያ፣ የቶል ዌይ ማለፊያ እንዲሁም በስራ ምክንያት የሚከፈሉ መግቢያ ትኬቶች ሁሉ በተሳፋሪው ይሸፈናሉ። ለስራ ቅልጥፍና ሲባል አሽከርካሪዎች ቅድሚያ ከፍለው መጨረሻ የሂሳብ መዝጊያ ላይ እነዚህን ወጭዎች መጨመር ይችላሉ።
  2. አባላት አንድ ሻንጣ በነፃ የሚጭኑ ሲሆን፣ ከ 1 በላይ ሻንጣ ለእያንዳንዱ 25 ብር የሚያስከፍሉ ይሆናል። ከጉዞ በፊት ለተሳፋሪው አሰራራችንን ማስረዳት አላስፈላጊ ጭቅጭቅን ያስወግዳል። ቅሬታ ካላቸው ወዲያው ወደ 8812 ደውለው ያሳውቁና የጥሪ ማዕከል ሰራተኞቻችን ተሳፋሪውን እንዲያስረዱ ያድርጉ። ሻንጣ ላልሆነ ማንኛውም ከ 25 ኪሎ በላይ የሚመዝን እቃ ብቻ አሽከርካሪው ከተሳፋሪው ጋር ተደራድሮ ለእቃው ማስከፈል ይችላል።
  3. አገልግሎታችንን በይበልጥ ለማስተዋወቅ እንዲረዳን ዘንድ ‘የራይድ ቅናሽ Coupon’ በአፕ ለሚታዘዙ ስራዎች በየግዜው እንበትናለን:: አሰራሩም- ይህ ኩፖን የደረሰው ሰው የPassenger አፕ ውስጥ በመግባት Promo በሚለው ክፍል ላይ ኮዱን አስገብቶ የተጠቀሰውን ያህል ቅናሽ ማግኘት ይችላል:: በግልባጭ ደግሞ ስራው የደረሰው አሽከርካሪ finish ሲጫን ሲስተሙ ጠቅላላ ሂሳቡን ያሳያል- ከዛ Comfirm ሲጫን በቅፅበት (automatically) ከቆጠረው ጠቅላላ ሂሳብ ላይ የኩፖን ዋጋውን ቀንሶ ለተሳፋሪው ቀሪውን እንዲከፍል ያሳያል (ሲስተሙ ኩፖን ቅናሽ እንዳለ የሂሳብ ዝርዝሩ ላይ ያሳያል):: ለአሽከርካሪው ደግሞ የተቆረጠውን ቅናሽ ወደ ክሬዲቱ automatically ያስገባል:: በስተመጨረሻ የገባውን ክሬዲት አሽከርካሪው ወዲያው Transaction History ላይ መመልከት ይችላል:: ያስተውሉ- በአፕ ቅናሽ የተሰጠን ሰው መልሶ ጨምሮ ማስከፈል ክልክል ነው::
  4. Cancellation Policy ። ከአቅምዎ በላይ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ያለ ምንም በቂ ምክንያት በ8812 ተለዋጭ ሰዉ እንዲላክ ሳያስተላልፉ cancel ማድረግ ሊያስጠይቅዎ ይችላል። የአገልግሎታችንን ጥራት ለማስጠበቅ ተሳፋሪን ከሚያጉላሉ ተግባራት እንዲቆጠቡ ይመከራል።
  5. ለአሽከርካሪው ደህንነት ሲባል ተሳፋሪ አብሮ ሳይጓጓዝ ምግብ፣ እቃ፣ ዶክመንት ማድረስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ተሳፋሪ አብሮ ከተጓዘ በኋላ የተጠቀመበትን ሂሳብ ወዲያው አወራርዶ ሂሳብ መዝጋት ይኖርበታል። ለተሳፋሪ ዱቤ መስጠት፣ ብር ማበደር ወይም በይደር ማስቀመጥ ከአሰራራችን ውጭ መሆኑን ተረድተው በሀላፊነት ያገልግሉ።
  6. የጠፋ እቃ ሲመልሱ ወይንም ምጥ ላይ ያለችን ሴት ወደ ሀኪም ቤት ሲያደርሱ ክፍያውን ራይድ ይከፍላል። ስራውን ከጨረሱ በኋላ በ 8812 ቢያሳውቁ እቃ ለመመለስ የ 100 ብር ቦነስ እና መምጥ ላይ ያለችን ሴት ለማድረስ የወጣውን ወጪ እንዲከፈልዎ መጠየቅ ይችላሉ። የስራ መደራረብ እንዳይከሰት ቢያንስ በ 72 ሰዓት ውስጥ እንዲያሳውቁን ይመከራል።
  7. የሚሸትና የመኪናዎን ጠረን በመጥፎ ሁኔታ የሚያውክ ወይም መኪናዎ የማይችለውን እቃ እንዲጭኑ አይገደዱም። በትህትና ተሳፋሪው ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ ነግረው መሰረዝ ይችላሉ።
  8. መኪና ውስጥ ማጨስ፣ መጠጣት ወይም ጫት መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ተሳፋሪም ሆነ አሽከርካሪ ከነዚህ ተግባራት እንዲቆጠብ ይመከራል። መኪናዎ በፊት በያዘዉ ግለሰብ ምክንያት የሲጃራ ሽታ ካለው ጥልቅ የሆነ ፅዳት በማድረግ ይተባበሩን።
  9. አላስፈላጊ አለመተማመንን ለማስወገድ ሁልግዜ ራይድ ሲያስጀምሩ ለተሳፋሪ ማሳየትን አይርሱ። በስራ ወቅት ስልክዎን ፊት ለፊት ከቴፕ አካባቢ ማስቀመጥ በይበልጥ ይመከራል

የአሽከርካሪ አፕ አጠቃቀም

የራይድን አፕ በአግባቡ ተረድቶ መጠቀም የአሽከርካሪዎቻችን ሀላፊነት ነው። በአሽከርካሪዎች አኘ ውስጥ የሚከተሉት ወሳኝ መጠቀሚያዎች ተካተዋል

  • ወደስራ መግቢያና መውጫ መጠቀሚያ (Online/Offline Switch)
  • Live የትራፊክ ሁኔታ መጠቆሚያ የቀለም ቅንብር
  • የስራ ፍሰት መጠቆሚያ (Heat Map)
  • ተሳፋሪ ጋር ወይም ወደመዳረሻ መጓዣ Navigation ወይም GPS
  • የስራ ክልል ርቀትን መመጠኛ
  • የራይድ ክሬዲት መፈተሻና ወደሌላ ሰው መላኪያ
  • የተሰሩ ስራዎች ሂሳብ ዝርዝር (Transaction History)
  • የተሰሩ ስራዎች የጉዞ መረጃ ዝርዝር (Recent Jobs)
  • የአሽከርካሪ የኮሚሽን እርከን (Driver Subscription Plan)
  • የአደጋ ግዜ ተጠሪ መደወያ
  • የስራ ምደባ ዝርዝር (Channels)
  • የቀጠሮ ስራ መዘርዘሪያ ገፅ (PreOrders)
  • የቀጠሮ ስራ ማብሪያ ማጥፊያ

ስለመጠቀሚያዎቹ በዝርዝር ለመማር ይህንን ይጫኑ

Share:

More Posts

2016 E.C. New Year Message from our CEO

የራይድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት:-

እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ:: መጭው ዓመት በሃገራችን የሰላም- የፍቅር እና የበረከት አመት እንዲሆን በመላው የራይድ ቤተሰብ ስም እየተመኘው- ቤተሰባዊ ወዳጅነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም በቀናነት የምንተሳሰብበት ዘመን እንሚሆን እምነቴ ነው:: ራይድ የሁላችንም ነው! ስለሆነም- በመጭው ዓመት አገልግሎታችንን ሙሉ ለሙሉ ሰው ተኮር በማድረግ በአለም ተወዳዳሪ የሆነና የአፍሪካ ኩራት የሆነ ጠንካራ ድርጅት በጋራ እንደምንገነባ እተማመናለሁ:: መልካም በዓል ከእነቤተሰብዎ እመኛለሁ::

RIDE Company Profile

Hybrid Designs PLC is a revolutionary Mobility technology company that aspires to implement simple, practical, and efficient mobility systems in Africa. Our

Send Us A Message

Scroll to Top